የጤና አገልግሎት ተደራሽነት...

ዝርዝር ዜና

አቃቂ ቃሊቲ ጤና ፅ/ቤት

የጤና አገልግሎት ተደራሽነት

ሚያዝያ 16-2018
ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

ለህብረተሰቡ ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ። አአ ጤና ቢሮ ሚያዚያ 9/2018ዓም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የ9ወር ስራ አፈፃፀም በጋራ ገምግመዋል። በግምገማ መድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ባስተላለፉት መልእክት ባለፉት 9 ወራት የከተማዋን ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን እና ለዉጦች መመዝገባቸዉን ገልፀዉ ቀሪ ወራት ይበልጥ ተጠናክረዉ በመቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል። በግምገማ መድረኩ የቢሮዉ የዘጠኝ ወር ስራ አፈፆፀም ሪፓርት በእቅድ እና በጀት ዳይሬክቶሬት ባለሞያ በሆኑት በአቶ ምስጋናዉ ሚካኤል ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል። በ9ወሩ በቢሮዉ በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባሮች የእናቶችና ህፆናት ጤናን ከመጠበቅ አንፆር ፣የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ፣በሽታ መከላከል፣ ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት፣ የመድሀኒትና ህክምና መሳሪያዋች አቅርቦት ስርጭት እና ሌሎች በቢሮዉ ተየሰሩ ስራዋች ላይ ጥልቅ ዉይይት ተደርጎበታል። የእናቶችና ህፆናትን ጤና ከመጠበቅ አንፆር የቤተሰብ እቅድ ተጠቃሚ ለማድረግ 428ሺ 8መቶ72 የሚሆኑ እናቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ከ100 ፐርሰንት በላይ ተግባራዊ ማድረግ ተችሏል ፣ የፓሊዮ መከላከያ ክትባት ከ826ሺ 8 መቶ በላይ ለሚሆኑ ህፆናት በመከተብ ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ተነግሯል ። በሽታን ከመከላከል እና ከመቆጣጠር አንፆር የቲቢ በሽታ ፣ የስኳር ፣ የማህፀን በር ካንሰር ፣ የደም ግፊት፣ ልየታና ህክምና አገልግሎት በታቀደው መሰረት የተከናወነ ሲሆን በ2030 ኤች አይ ቪን ስርጭትን ለመግታት ሶስቱን ዘጠና አምስት ከማሳካት አንፆር በሽታዉ ያለባቸዉን ሰዎችን ፈልጎ ከማግኘት አንፆር 88 በመቶ ፣ በሽታዉ የተገኘባቸዉን ART ህክምና እንዲጀምሩ ከማድረግ አንፆር 95በመቶ እንዲሁም ART ህክምና እንዲጀምሩ ከተደረጉት መካከል የቫይረስ መጠንን 98 በመቶ መቀነስ መቻሉ በቀረበው ሪፖርት ተመልክቷል ። ህክምና አገልግሎትን በተመለከተ የተመላላሽ ህክምና በ9 ወሩ 13 ሚሊየን 821ሺ በላይ ታካሚዎች አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን ከ2መቶሺ በላይ ለሚሆኑ ታካሚዎች የአስተኝቶ ህክምና መስጠት ተችሏል። የፋርማሲ አገልግሎት በተመለከተ በጤና ተቋማት መሰረታዊ የመድሀኒት አቅርቦት 97 በመቶ መድረስ መቻሉን እንዲሁም በሀኪም የታዘዙ መድሀኒቾችን ማግኜት 94 በመቶ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል። የወረቀት አልባ የጤና አገልግሎ ተደራሽ ከማድረግ አንጻር 69 ጤና ጣቢያዎችን እና ሁሉንም ሆስፒታል በዲጂታል (EMR) አገልግሎ እንዲሰጡ ተደርጓል ። የበማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህንአባላትን ከማፍራት እና የስርአቱ ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር በ9 ወሩ ውስጥ 70ሺ 6መቶ 98 አዲስ አባል ማፍራት በመቻሉ አጠቃላይ 2 ሚሊዮን 700 ሺህ በላይ የበማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ አባላት እንደሚገኙ በሪፓርቱ ተገልጿል። የቢሮዉ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ሀንጋቱ መሀመድ በጤናዉ ዘርፍ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶች ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻሉላ እና እየዘመኑ መምጣታቸዉን ገልፀዉ ባለፍት 9 ወራት እንደከተማ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ዉጤት የተመዘገበበት መሆኑን እና ይሄንንም ዉጤት ለማስቀጠል በትኩረት ልንሰራ ይገባል ብለዋል። በቢሮዉ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ ወቅቱ የሚጠይቀዉን የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራቶች አበረታች መሆናቸዉን ገልፀዉ ይሄንንም ለማስቀጠል ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።